ስንፈተ ወሲብ | የጓዳ ችግሮች
ስንፈተ ወሲብ በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። በተለይም በወጣቶች ላይ ሲከሰት የተለያየ ስነ ልቦናዊ ጫና ያስከትላል። ዶ/ር ሃና የተወሰኑ መረጃዎችን ታጋራናለች። የጤና ባለሙያዎችን ለማማከር 9394 ላይ ይደውሉልን በ WeCare Et መተግበሪያ ሃኪሞችን ለማማከር 👇👇 https://play.google.com/store/apps/de... ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ሌሎች ማህበራዊ ገጾቻችን ይጎብኙ። 📌 Telegram: https://t.me/WeCareET 📌 Facebook፡ https://www.facebook.com/WeCareET/
Wecare Digital Health
3 months ago
1
Wecare Digital Health
5 months ago
🇪🇹 እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ 🇪🇹 👩‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ስፔሻሊስት ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394/ 0964686464 ላይ ይደውሉ ። #wecareet #adwavictory #አድዋ #ኢትዮጲያ #ጀግኖች #notcolonized #9394 #ethiopian #healthcare
3
Wecare Digital Health
6 months ago (edited)
🚨በቂ ውሃ አለመጠጣት ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል ያውቃሉ ? 🩺🩺ጥናቶች እደሚያሳዩት አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ሁለት ሊትር ውሃ መጠጣት አለበት። ነገር ግን በሙቀት እና በሌሎች የጤና ሁኔታዎች ምክንያት በቀን ውስጥ የሚያስፈልገው የውሃ መጠን ከፍ ወይም ዝቅ ሊል ይችላል። 👉👉በቂ ውሃ የመጠጣት 7 በሳይንስ የተረጋገጡ የጤና ጥቅሞች 📌የአካል ብቃትን ከፍ ለማድረግ ይረዳል 📌የአንጎል ተግባርን በእጅጉ ያግዛል 📌ራስ ምታትን ለመከላከል እና ለማከም ይረዳል 📌የሆድ ድርቀትን ለማስተካከል ይረዳል 📌የኩላሊት ጠጠርን ለማከም ያግዛል 📌ስካር ቶሎ እንዲለቅ ይረዳል 📌ክብደት ለመቀነስ ያግዛል 👩🏽‍⚕️ሰውነታችን 60 % ውሃ እንደመሆኑ መጠን የተቀላጠፈ እና ጤናማ የአእምሮ እና የአካል ተግባር እንዲኖር ለማድረግ በቂ ውሃ መጣቶን እንዳይዘነጉ ። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #wecare #doctors #hakim #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor#9394 #children #feeding #water #drinking #drinkingwater
Wecare Digital Health
6 months ago
🚨 የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሀገራቸን ከጡት ካንሰር ቀጠሎ ሁለተኛው የእናቶች ገዳይ በሽታ ነው በአለም ላይ ደግሞ በዓለም ላይ አራተኛው ገዳይ የካንሰር ዓይነት ነው። የማኅጸን በር ጫፍ ካንሰር በሃገራችን በየዓመቱ 4000 ሺህ በላይ ሴቶችን ይገድላል። የማህጸን በር ካንሰር ከካንሰሮች ሁሉ 100% መከላከል የምችለው የካንሰር አይነት ሲሆን የተለያዩ ጥናቶች ኤች-ፒ-ቪ (HPV) በሚል ምሕጻር የሚጠራው ቫይረስ መከላከያ ክትባት 97 ከመቶ የማኅጸን በር ጫፍ ካንሰርን እንደሚከላከል ያሳያሉ። 👉የማህጸን በር መከላከያ (HPV) ክትባት ዘጠኝ ዓይነት ኤች-ፒ-ቪ ቫይረስን ይከላከላል። ከእነዚህ መካከል ሁለቱ የ HPV አይነቶች፣ HPV 16 እና 18 የማኅጸን በር ጫፍ ካንሰርን የሚያመጡ ናቸው። የፊንጢጣ ካንሰር እና የመራቢያ አካላት ካንሰር እንዲሁም የጭንቅላት እና የአንገት ካንሰር ሌሎቹ ናቸው። 🚨 ክትባቱ ለነማን ይሰጣል? የማህፀን በር ካንሰር ክትባት እድሜያቸው ከ9+ በላይ ለሆኑ ልጃገረዶች እና ወንዶች ልጆች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የካንሰር ክትባት ነው። ሴት እና ወንድ ታዳጊዎች ከግንኙነት በፊት ቢወስዱት ቀደም ብለው ለኤችፒቪ ከመጋለጣቸው በፊት ክትባቱን ቢወስዱ ይመከራል። ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት ክትባቱ ኢንፌክሽንን ስለሚከላከል ነው። ሰውነት አንዴ በዚህ ኢንፌክሽን ከተጠቃ ግን ክትባቱ ቫይረሱን ከሰውነት የማስወገድ አቅም የለውም። ቫይረሱ በጣም ተዛማጅ ስለሆነ ክትባቱ ወጣቶች ለወሲብ ግንኙነት ዝግጁ ከመሆናቸው በፊት ቢሰጣቸው መልካም ነው። 🚨 ክትባቱ እንዴት ይሰጣል እስከመቼስ ይቆያል ? ክትባቱ በመርፌ በኩል በእጃችን ጡንቻ የሚሰጥ ሲሆን ፣ የአንድ ግዜ ክትባት ለ10 አመት ቫይረሱን የመከላከል አቅም አለው ። 🚨የ HPV ክትባት የተከተቡ ሴቶች የማህጸን በር ቅድመ ካንሰር (pap smear ) ምርመራ ማድረግ አለባቸው? አዎ፣ የ ኤች ፒ ቪ ክትባት የተከተቡ ሴቶች አሁንም መደበኛ የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም ክትባቱ ሰውነታችሁን ከ HPV እና ከማኅጸን ጫፍ ካንሰር የሚከላከለው ሲሆን ነገር ግን በማህፀን በር ጫፍ ላይ ወደ ማህፀን በር ካንሰር የሚወስዱትን ሌሎች ለውጦችን ስለማይከላከል ነው። መደበኛ የማህጸን በር ምርመራዎች የማህጸን በር ለውአጦች ወደ ካንሰር ከመለወጣቸው በፊት እንዲገኙ እና 100 % እንዲታከሙ እና ካንሰርንም ለመከላከል ያግዛሉ ። 🚨ኤች- ፒ- ቪ ምንድነው? ኤች-ፒ-ቪ (HPV) በሚል ምሕጻር የሚጠራው ይህ ቫይረስ በሙሉ ስሙ ሂውማን ፓፒሎማቫይረስ (human papillomavirus) ይሰኛል። ከመቶ በላይ የቫይረሱ ዓይነቶች አሉ። ኢንፌክሽኖች ታዲያ ምንም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ቆዳ ላይ ትንንሽዬ እብጠቶች የሚታዩበት አጋጣሚ አለ። እነዚህ ቆዳ ላይ ኩፍ የሚሉ ምልክቶች ታዲያ በእጅ፣ በእግር፣ በመራቢያ አካል እና በአፍ ውስጥ ሊከሰቱ ይችላሉ። ደም የተቀላቀለበት ሽንት፣ ከማረጥ በኋላ የሚከሰት የደም ፍሰት፣ ያለ ጊዜው በወር አበባ መሀል የሚመጣ የደም መፍሰስ፣ ብሽሽት አካባቢ የህመም ስሜት ከታየ ሐኪም መጎብኘት ይመከራል። ብዙ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሳያውቁ ሰውነታቸው በራሱ ጊዜ ቫይረሱን ሊያስወግደው ይችላል። ይሁንና ከፍተኛ የሚባለው የኤችፒቪ ዓይነት ወደ ካንሰር ሊያድግ የሚችል ነው። 🚨ቫይረሱ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ይተላለፋል? አዎ ይተላለፋል። በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ቫይረስ ነው። በቀላሉ የቆዳ ለቆዳ ንክኪም ይተላለፋል። ከ80 በመቶ በላይ ሰዎች ገና 25 ዓመት ሳይሞላቸው ለኤችፒቪ ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ። ብዙ ሰዎች ከ18 ወራት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ በቫይረሱ ይጠቃሉ። ነገር ግን ቫይረሱ የተራክቦ በሽታ ነው ለማለት ይቸግራል። ምክንያቱም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ በሚፈጠር ፈሳሽ ልውውጥ የሚተላለፍ ስላልሆነ። ቢሆንም ግን ቫይረሱ በወሲብ ጊዜ በሚደረግ የቆዳ ለቆዳ ንክኪ ሊተላለፍ መቻሉ አደገኛ ያደርገዋል። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #wecareet #freeconsultaion #cervicalcancer #cancer #womenhealth #prevention #ነጻ #safemotherhood #woman #motherhood #cervical cancer#telemedicine #healthcare #midwifes #drbethel #ዶክተር #wecare #doctors #homecare #wecareet #healthcare
Wecare Digital Health
11 months ago
🌻እንኳን ለ አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ !🇪🇹 🫵 ልዩ የሴቶች የነጻነት ቀን የሆነውን አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓልን በማስመልከት ለሴት እህቶቻችን እና እናቶች የ10% ቅናሽ ለማህጻን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ እና ለማህጻን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር ምክክር አዘጋጅተናል። 🚨ዛሬውኑ የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን በ9394 ላይ ይደውሉ ። 🗣ቅድመ ምርመራ በማድረግ በ100 % መከላከል የምንችለውን የማህጸን በር ካንሰር ይከላከሉ። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #Ashenda #ashenda2024 #shadey #wecareet #doctors #cervicalcancer #cancer #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394#Ethiopian #habesha
2